Get In Touch
Bole, Africa Avenue Addis Ababa Ethiopia
Email info@orointbank.com
Ph: + 251 115 572 002
P.O.Box: 27530/1000 Addis Ababa,Ethiopia
Fax: + 251 115 572 002
SWIFT CODE: ORIRETAA

ማህበራት – ሆለታ

ኦሮሚያ ባንክ በሆለታ ከተማ ባካሄደዉ ማህበራትን ያማከለ የገበያ እና የተደራሽነት ንቅናቄ 400 ለሚሆኑ አርሷደሮች ለክርምት የግብርና ስራ የሚያግዛቸዉን መጫሚያ አበረከተ፡፡

በሆለታ ከተማ በተካሄደዉ ማህበራትን ያማከለ የገበያ እና የተደራሽነት ንቅናቄ ወልመራ ወረዳ ስር የሚገኙ ከተለያዩ ቀበሌዎች የተወጣጡት በማህበር የታቀፉ አርሷደሮች ተገኝተዋል፡፡

ባንካችን ማህበራዊ ላፊነቱን ለመወጣት ለክረምት የግብርና ስራ የሚያገለግላቸዉን ቦት ጫማ ከማበርከቱም በተጨማሪ የማህበራትን እና አባላቱን አቅም የሚያጎለብት  ለየት ያለ የባንክ አገልግሎት ለአርሷደሮቹ አስተዋዉቋል፡፡

ይህ ከባንካች የቀረበዉ  የማህበራትን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ የባንክ አገልግሎት ለማህበራቱ ማነቆ የሆኑ ጉዳዮችን በመፍታት በርካታ የፋይናንስ አማራጮችን ይዞ ቀርቧል፡፡

ኦሮሚያ ባንክ አርሷደሩን ያማከለ በርካታ የፋይናንስ አማራጮች በማቅረብ ለሀገራችን የግብርና እድገት በጎ አስተዋዕፆ እያበረከተ እንደሚገኝ ይታወቃል።