Get In Touch
Bole, Africa Avenue Addis Ababa Ethiopia
Email info@orointbank.com
Ph: + 251 115 572 002
P.O.Box: 27530/1000 Addis Ababa,Ethiopia
Fax: + 251 115 572 002
SWIFT CODE: ORIRETAA

አሮሚያ ባንክ በአዋሳ ከተማ በተካሄደዉ 40ኛዉ የሻምበል አበበ ቢቂላ ማራቶን ዉድድር ዋና አጋር መሆኑን ሲገልፅ ታለቅ ደስታ ይሰማዋል፡፡

ኦሮሚያ ባንክ ቀልጣፋ እና ዘመናዊ የባንክ አገልግሎት ከመስጠት ባሻገር የሀገራችንን ስም እና ሰንደቅ አላማ በአለም አደባባይ ከፍ አድርገዉ የሚያሳዩ ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት የስፓርቱን ዘርፍ እየደገፈ ይገኛል፡፡ በዉድድሩ ላይ ባንካችን ከእስፓርት ቤተሰቡ እና ከአዋሳ ከተማ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር የመገናኘት እድል በማግኘት ምርት እና አገልግሎቶቹን አስተዋዉቋል፡፡

በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት የተካሄደዉ 40ኛዉ የሻምበል አበበ ቢቂላ ማራቶን ዉድድር በሁለቱም ፆታ ኦሮሚያ ፓሊስ ስፓርት ክለብ የበላይነቱን የወሰደ ሲሆን በወንዶች ጎሳ አምሳሉ እና በሴቶች ኩረኒ ጀሊላ አሸናፊ ሆነዋል፡፡

በዉድድሩ ላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ክብርት ረዳት ኮሚሺነር ደራርቱ ቱሉን ጨምሮ የኦሮሚያ ባንክ እና የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ባንካችን በቀጣይም መሰል ዉድድሮችን በመደገፍ ለሀገራችን መልካም ስም እና ዝና ላይ በበጎ መልኩ ተፅዕኖ በሚፈጥሩ ስራዎችን አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡