Get In Touch
Bole, Africa Avenue Addis Ababa Ethiopia
Email info@orointbank.com
Ph: + 251 115 572 002
P.O.Box: 27530/1000 Addis Ababa,Ethiopia
Fax: + 251 115 572 002
SWIFT CODE: ORIRETAA

ኦሮሚያ ባንክ በስራ እድል ፈጠራ ዘርፍ በሀገር ደረጃ ባሳደረው በጎ ተፅዕኖ ላይ የጋዜጠኞች የመስክ ጉብኝት ተካሄደ፡፡

ጉብኝቱን አስመልክቶ የኦሮሚያ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኦቦ ተፈሪ መኰንን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

እንደ ዋና ስራ አስፈፃሚ ገለፃ ኦሮሚያ ባንክ በሀገር ደረጃ ካሳረፋቸዉ መልካም አሻራዎች መካከል ባንኩ ቀጥሯቸዉ ከሚያሰራቸዉ ከ11 ሺ በላይ ቋሚና ጊዜያዊ ሰራተኞች በተጨማሪ በሚከተለዉ የብድር መሪ እቅድ ፤ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለበርካታ ሺ የሀገራችን ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠር ችሏል ብለዋል፡፡

በባንካችን የብድር መሪ ዕቅድ መሰረት ግለሰቦችም ሆነ ድርጅቶች ከባንካችን የብድር አገልግሎት ሲያገኙ የስራ አዋጭነት ከመገምገም በተጨማሪ ለምን ያህል ዜጎች የስራ ዕድል ይፈጥራሉ የሚለዉ ጉዳይ ከፍተኛ ትኩረት ይሰጠዋል ያሉት ኦቦ ተፈሪ፤ በዚህም ባንኩ በሀገራችን የስራ አጥነት ችግርን ለመቅረፍ ጉልህ አስተዋዕፆ እያበረከተ እንደሚገኝ በአፅዕኖት ገልፀዋል፡፡

ኦቦ ተፈሪ አክለዉም ባንካችን በተለያዩ የሀገራችን ከተሞች የተደራጁ ጥቃቅን እና አነስተኛ ማህበራት እንዲሁም ለስራ ፈጣሪዎች (ለእንተፕርነሮች) በፋይናንስ አያያዝ እና አስተዳደር ላይ ስልጠና እና የብድር አቅርቦት በመስጠት የበርከታ ማህበራትን አቅም እያጎለበተ እንደ ሚገኝ ጠቁመዋል፡፡

ባንኩ እያስገነባቸው ካሉት ግዙፍ ፕሮጀከቶች መካከል የመሸጋገሪዉን ዋና መስራያ ቤት እና በ20 ሄክታር መሬት ላይ ከሚገነባዉ የገላን የልህቀት እና የኮንቬንሽን ማዕከል ግንባታ ስራዎች ለብዙ ሺ ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠራቸዉን ኦቦ ተፈሪ አስረድተዋል፡፡