Get In Touch
Bole, Africa Avenue Addis Ababa Ethiopia
Email info@orointbank.com
Ph: + 251 115 572 002
P.O.Box: 27530/1000 Addis Ababa,Ethiopia
Fax: + 251 115 572 002
SWIFT CODE: ORIRETAA

ኦሮሚያ ባንክ የትንሳዔን በዓል ምክንያት በማድረግ ለ3 ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች የገንዘብ ድጋፍ አደረገ፡፡

በኦሮሚያ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኦቦ ተፈሪ መኰንን የተመራዉ የባንካችን የላዕላይ ስራ ኃላፊዎች የመቄዶኒያ የአረጋዊያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከልን ጎብኝተዋል፡፡

በማዕከሉ በተካሄደዉ የድጋፍ መርሐ-ግብር ለመቄዶኒያ የአረጋውያን እና የአዕምሮ ህሙማን ማዕከል 1 ሚሊዮን ብር፣ ለአበበች ጎበና የበጎ አድራጎት ድርጅት 1 ሚሊዮን ብር እና ለጌርጌሴኖን የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማህበር 1 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደርጓል፡፡

የኦሮሚያ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኦቦ ተፈሪ መኰንን ኦሮሚያ ባንክ የተቀላጠፈ ዘመናዊ የባንክ አገልግለት ከመስጠት በተጨማሪ ተቋማዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ለሰብዓዊ ሥራዎች ቅድሚያ ሰጥቶ እየሰራ ነዉ ብለዋል፡፡ መቄዶኒያ የአረጋውያን እና የአዕምሮ ህሙማን ማዕከል ክቡር ለሆነዉ የሰዉ ልጅ እያከናወናቸዉ ያለዉ ሁለንተናዊ ህይወትን የማስቀጠል ስራዎች እጅግ የሚያኮሩ መሆኑን አዉስተዉ ባንኩም ሁሌም ከማዕከሉ ጎን እንደሚቆም አረጋግጠዋል፡፡

የመቄዶኒያ የአረጋውያን እና የአዕምሮ ህሙማን ማዕከል መስራች እና ስራ አስኪያጅ የክብር ዶ/ር ቢኒያም በለጠ የኦሮሚያ ባንክ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ማዕከሉን በመጎብኘታቸዉ እጅግ መደሰታቸዉን ገልፀዉ በቀጣይም ባንኩ ለማዕከሉ የሚያደርገዉን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የአበበች ጎበና የበጎ አድራጎት ድርጅት ስራ አስኪያጅ አቶ እሸቱ አረዶ እና የጌርጌሴኖን የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማህበር ምክትል ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ዘነበ አለሙ ለተደረገላቸዉ ድጋፍ ኦሮሚያ ባንክን አመስግነዋል፡፡

ኦሮሚያ ባንክ በዚህ ወር ብቻ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት 8 ሚሊዮን ብር ወጪ በማድረግ ለተለያዩ ሀገር በቀል ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ድጋፍ አድረጓል፡፡