Get In Touch
Bole, Africa Avenue Addis Ababa Ethiopia
Email info@orointbank.com
Ph: + 251 115 572 002
P.O.Box: 27530/1000 Addis Ababa,Ethiopia
Fax: + 251 115 572 002
SWIFT CODE: ORIRETAA

ኦሮሚያ ባንክ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባዘጋጀው የሐዋላ ፍሰት ግንዛቤ ማስጨበጫ አውደ ርዕይ ላይ ተሳትፏል።

ባንካችን ከሀገር ውጭ ለሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያዊያንን ማዕከል ያደረጉ የባንክ አገልግሎቶችን ለአውደ ርዕይው ተሳታፊዎች አስተዋውቋል።

በእስካይላይት ሆቴል በተዘጋጀው አውደ ርዕይ ላይ የብሔራዊ ባንክ ገዢ አቶ ማሞ ምህረቱ ፣ የባንካችን ዋና አስፈፃሚ አቶ ተፈሪ መኰንን ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖን ጨምሮ የበርካታ ባንኮች ከፍተኛ ዓመራሮች እንዲሁም በውጭ ሀገር የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ተሳትፈዋል።

ኦሮሚያ ባንክ ዜጎቻችን ከባህር ማዶ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ከእኛ ጋር በሚሰሩ ገንዘብ አስተላላፊ ወኪሎች በኩል የሚልኩትን የውጭ ሀገር ገንዘብ በታማኝነት በማድረስ መልካም ስም አፍርቷል።

በተጨማሪም ባንኩ የዲያስፓራውን ማህበረሰብ በልዩነት ተጠቃሚ የሚያደርጉ በርካታ የባንክ አገልግሎቶች ቀርፆ ተግባራዊ እያደረገ ነው።