Get In Touch
Bole, Africa Avenue Addis Ababa Ethiopia
Email info@orointbank.com
Ph: + 251 115 572 002
P.O.Box: 27530/1000 Addis Ababa,Ethiopia
Fax: + 251 115 572 002
SWIFT CODE: ORIRETAA

የባንካንችን የንግድ ምልክት አርማ የሆነዉ ግዙፉ እና ባለ ግርማ ሞገሱ የፈረስ ቅርፅ ቦሌ መንገድ በሚገኘዉ የኦሮሚያ ባንክ ዋና መስሪያ ቤት ተመረቀ፡፡

ከተለያዩ የብረታ ብረት ምርቶች የተሰራዉ ባለ ግርማ ሞገሱን የፈረስ አርማ መርቀዉ የከፈቱት የባንካችን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተፈሪ መኮንን፤ ይህ የጥበብ ስራ የባንካችንን አርማ በልዩ ሁኔታ ከማስተዋወቅ በተጨማሪ፤ ለመዲናችን የኮሪደር ልማት ተጨማሪ ዉበት ፈጥሯል ብለዋል፡፡

የቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 1 ስራ አስፈፃሚ አቶ አበራ አለሙ በበኩላቸው ቦሌ መንገድ የሀገር ዉስጥ እና የዉጭ ሀገር እንግዶች እና ጎብኚዎች በብዛት የሚመላለሱበት ስለሆነ፤ ኦሮሚያ ባንክ ከኮሪደር ልማቱ ጋር የተጣጣመ፣ ከተማችንን የሚመጥን እና ጥራቱን የጠበቀ የእንግዶች የአይን ማረፊያ ቀርፅ በመስራቱ ኩራት ይሰማናል ብለዋል።

ቦሌ መንገድ ላይ በሚገኘዉ የባንካችን ዋና መስሪያ ቤት ጎን የቆመዉ አና በሁለት እግሮቹ ከፍ ብሎ የሚታየዉ ባለ ግርማ ሞገስ የፈረስ ቅርፅ 4 ሜትር ተኩል ርዝማኔ ያለዉ ሲሆን ከ700 ኪሎ ግራም በላይ ይመዝናል፡፡