Get In Touch
Bole, Africa Avenue Addis Ababa Ethiopia
Email info@orointbank.com
Ph: + 251 115 572 002
P.O.Box: 27530/1000 Addis Ababa,Ethiopia
Fax: + 251 115 572 002
SWIFT CODE: ORIRETAA

የኦሮሚያ ባንክ የገበያ እና የተደራሽነት ንቅናቄ በቱሉ ቦሎ ከተማ በደማቅ ሥነ-ሥርዓት ተካሄደ።

ባንካችን በዚህ በዓይነቱ ልዩ የሆነና አርሶ አደሩን ያማከለ መርሐ ግብር ላይ ከ400 በላይ ለሚሆኑ አርሶ አደሮች ለክረምት ስራ የሚሆን ቦት ጫማዎችን በማበርከት ሁኑኛ አጋር መሆኑን አስመስክሯል።

የባንካችን የዋና ስራ አስፈፃሚ አማካሪ ኦቦ እንዳለ ፎዬ ባስተላለፉት መልዕክት ኦሮሚያ ባንክ እንደምን ጊዜውም ከህዝብ ጎን በመቆም የልማት አለኝንታነቱን በተግባር ያስመሰከረ የህዝብ ባንክ መሆኑን አውስተው፤ የተከናወነው መርሐ ግብር ለዚህ ዋቢ መሆኑን ጠቁመዋል። አክለውም ከዚህ ቀደም የአጨዳ ወቅትን በማስመልከት በደንዲና በሌሎች ወረዳዎች በአጠቃላይ ከ8000 በላይ ማጭዶችን ለአርሶአደሮች ማከፋፈሉን አስታውሰው በዚህ በልዩ ሁኔታ ለአርሶአደሮች የተዘጋጀውን ይህንን አገልግሎት በመጠቀም ከባንኩ ጋር ተቀራርበው እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።

በዚህ ደማቅ ሥነ-ሥርዓት ላይ የበቾ ወረዳ አስተዳዳሪ ኦቦ ንጉሴ ፈንታ፣ የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ መገርሳ አራርሳን ጨምሮ በርካታ የቱሉ ቦሎ ነዋሪዎች እና የበቾ ወረዳ አርሶ አደሮች ተገኝተዋል።

አስተዳዳሪው ባስተላለፉት መልዕክት ባንኩ በተለየ ሁኔታ አርሶ አደሩን ማዕከል ያደረጉ ግብዓቶችን ተደራሽ ማድረጉ ከሌሎች ባንኮች በተለየ ለአርሶአደሮች ቅርብ መሆኑን የሚያመላክት መሆኑን ጠቅሰው ለዚህም ጊዜውን የዋጀ አበርክቶት ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበው ማህበረሰቡ ከባንኩ ጋር እንዲሰራና ከባንኩ ጋር በጋራ እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።

የባንካችን የ15 ዓመታት ስኬታማ ጉዞን ጨምሮ ባንኩ ስለሚሰጣቸው ምርት እና አገልግሎቶች ለተሳታፊዎች ገለፃ ተደርጓል።