የኦሮሚያ ባንክ 7ኛዉ ዓመታዊ የችግኝ ተከላ መርኀ-ግብር ገላን ክ/ከተማ በሚገኘዉ በባንኩ የልህቀት እና ኮንቬንሽን ማዕከል ተካሄደ፡፡
በዚህ የችግኝ ተከላ መርኀ- ግብር ላይ የባንኩ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችን፣ የፊንፊኔ ከተማ ቀጠና ጽ/ቤት ዳይሬክተሮች እና የቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆችን ጨምሮ የገላን ክ/ከተማ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
የኦሮሚያ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኦቦ ተፈሪ መኮንን ባስተላፉት መልዕክት ባንካችን ላለፉት 7 ዓመታት ሰራተኞቹን በማሳተፍ በችግኝ ተከላ መርኃ- ግብር ላይ በስፋት ሲሳተፍ መቆየቱን አስታዉሰዉ በቀጣይም ባንኩ በሀገራዊ ጉዳች ላይ በንቃት መሳተፉን ይቀጥላል ብለዋል፡፡
በዚህ የችግኝ ተከላ መርኃ-ግብር የተሳተፊ የኦሮሚያ ባንክ የስራ ዓመራር አባላት እና የገላን ክፍለ ከተማ የስራ ሀላፊዎች በባንኩ እየተገነባ ያለዉን የልህቀት እና የኮንቬንሽን ማዕከል ሁለተኛዉን ምዕራፍ ግንባታ ጎብኝቷል፡፡