1. News and Updates
  2. ባንካችን ኦሮሚያ ባንክ ለተከታታይ 3ኛ ጊዜ የአውሮፓ ሶሳይቲ ፎር ኳሊቲ ሪሰርች (ESQR) የ2024 ዓለም-አቀፍ የጥራት ተሸላሚ መሆኑን አስመልክቶ የባንካችን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኦቦ ተፈሪ መኰንን ለብዘሃን መገናኛ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ለተከታታይ 3ኛ ጊዜ የአውሮፓ ሶሳይቲ ፎር ኳሊቲ ሪሰርች (ESQR) የ2024 ዓለም-አቀፍ የጥራት ተሸላሚ

ኦሮሚያ በንክ እያስመዘገበ ያለው የማይዋዥቅ የላቀ አገልግሎት ለዚህ ዓለም-አቀፍ እዉቅና ምክንያት መሆኑን የባንካችን ዋና ስራ አሰፈጻሚ አብራርተዉ፤ በተግዳሮቶች ዉስጥ ይህንን ሽልማት ማግኘታችን ለመላዉ የባንካችን ማህበረሰብ ትልቅ ኩራት መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

የአውሮፓ ሶሳይቲ ፎር ኳሊቲ ሪሰርች (ESQR) ህዳር 30/2017 ዓ.ም በኦስቲሪያ ቪየና ባዘጋጀዉ ዓለም-አቀፍ ኮንቬንሽን ላይ ባንካችን የነበረዉን ተሳትፎ ያብራሩት ኦቦ ተፈሪ፤ በመረሃ-ግብሩ ላይ ተስሸላሚ መሆናችን ባንካችንን ብቻ ሳይሆን ሀገራችንን በመወከል፤ ኢትዮጵያ እየተገበረችዉ ያለዉን ሁለንተናዊ የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ያስተዋወቅንበት መድረክ ነዉ ብለዋል፡፡

ከኢትዮጵያ ኦሮሚያ ባንክን ጨምሮ ከሁሉም ክፍለ ዓለማት የተወጣጡ  41 ሀገራት እና 49 የተለያዩ ተፅዕኖአቸው የጎሉ ስመጥር የቢዝነስ እና መንግስታዊ ተቋማት እውቅና ማግኘታቸዉን ያስታወሱት ኦቦ ተፈሪ፤ ባንካችን ወደ ዓለም አደባባይ በሰፋት በመዉጣት ተወዳጅ ዓለም-አቀፍ  ብራንድ እየሆነ መምጣቱን አስገንዝበዋል፡፡

በተጨማሪም ከዋና ዋና የአፈፃጸም ስኬቶች ባሻገር ባንካችን ጤናማ ባንክ መሆኑን ያወሱት አቶ ተፈሪ፣ ለዚህ ተከታታይ እና እመርቂ ስኬት ሁሉንም ባለድርሻዎች፣ የባንካችን የስራ ዓመራር ቦርድ፣ ማኔጀመንት እና መላዉን የባንካችን ሰራተኞችን ኦቦ ተፈሪ አመስግነዋል፡፡

Pin It on Pinterest

Share This

Share This

Share this post with your friends!

Share This

Share this post with your friends!

×