ኦሮሚያ ባንክ ቀልጣፋ እና ዘመናዊ የባንክ አገልግሎት ከመስጠት ባሻገር የሀገራችንን ስም እና ሰንደቅ አላማ በአለም አደባባይ ከፍ አድርገዉ የሚያሳዩ ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት የስፓርቱን ዘርፍ እየደገፈ ይገኛል፡፡ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት የተካሄደዉ ይህ ዉድድር ለስድስት ቀናት ሲካሄድ የቆየ ሲሆን ለሀገራችን አዲስ የሆነዉ Time Tronics የተሸኘ ቴክኖሎጂ ስራ ላይ አዉሏል።
ዉድድሩ መጋቢት 20 ቀን 2018 ዓ.ም. ፍጻሜዉን ያገኘ ሲሆን በመዝግያ ስነ ስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህንን ጨምሮ የኦሮሚያ ባንክ እና የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል፡፡ ባንካችን በቀጣይም መሰል ዉድድሮችን በመደገፍ በሀገራችን መልካም ስም እና ዝና ላይ በበጎ መልኩ ተፅዕኖ የሚፈጥሩ ስራዎችን አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

