ግራንድ አፍሪካን የተቋማትና የአመራር ሽልማት
ግራንድ አፍሪካን የተቋማትና የአመራር ሽልማት ድርጅት ባንካችንን ኦሮሚያ ባንክ እና የባንካችንን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኦቦ ተፈሪ መኮንን በአፍሪካ የኢንደስትሪ ልማት ልዩ ምዘና የተቋም ስኬት እና የአመራር ልህቀት የ2017 ዓ.ም ከፍተኛ የክብር ሽልማት ከነግዴታዉ፤ ጥቅሙ እና ሙሉ ክብሩ ጋር ሸልሟል፡፡
ለዉጤታማ ተቋማት እዉቅና በመስጠት የሚታወቀዉ ግራንድ አፍሪካን የተቋማትና የአመራር ሽልማት ድርጅት፤ ኦሮሚያ ባንክ በ2017 ዓ.ም በኢንደስትሪዉ ባስመዘገበዉ ዉጤት እና ተግባራት፥የተቋም ልህቀት ከፍተኛ የክብር ዲፕሎማ ሽልማት (Diploma of Organizational Excellence Award) ተሸላሚ ሆኗል፡፡
በዚህ የሽልማት ሥነ-ሥርዓት ላይ የባንካችን ዋና ስራ አስፈፃሚ ኦቦ ተፈሪ መኮንን በባንካቸዉ ላሳዩት የአመራር ልህቀት እና ሁለንተናዊ ዉጤታማነት ምሳሌ በመሆን፥ ከግራንድ አፍሪካን የተቋማትና የአመራር ሽልማት ድርጅት የበላይ ጠባቂ እና ከቀድሞ የኢ.ፌ.ድ.ሪ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ እጅ የኮርዶን፤ ኒሻን እና ከፍተኛ የክብር ዲፕሎማ (Diploma of Leadership Excellence) ተቀብለዋል፡፡
በአድዋ ድል መታሰቢያ ፓን አፍሪካ አዳራሽ በተካሄደዉ ደማቅ የእዉቅና እና የሽልማት ሥነ-ሥርዓት ላይ በርካታ ለሀገራችን እድገት ከፍተኛ አስተዋዕፆ እያበረከቱ የሚገኙ ተቋማት እና የተቋማት መሪዎች የተሸለሙ ሲሆን፤በዚህ መርኃ-ግብር ላይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች እና ታዋቂ ግለሰቦች ተገኝተዋል፡፡

