1. News and Updates
  2. ኦሮሚያ ባንክ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ኳንተም ቴክኖሎጂ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።

ስምምነቱን የፈረሙት የኦሮሚያ ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተፈሪ መኮንን፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የንግድ ሥራ ዘርፍ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ለማ ያዴቻ እና የኳንተም ቴክኖሎጂ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ሶፎንያስ እምቢበል ናቸዉ።

የባንካችን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኦቦ ተፈሪ መኮንን በስምምነቱ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ የሀገር ኩራት ለሆነዉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ደንበኞችን ጉዞ ለማሳለጥ ኦሮሚያ ባንክ ሚልኪ ዲጂታል የብድር አገልግሎት አቅርቧል ብለዋል፡፡ ሚልኪን የሚጠቀሙ መንገደኞች ያለምንም ማስያዣ ከአየር መንገዱ ትኬታቸዉን ከቆረጡ እና ከበረሩ በኋላ ተረጋግተዉ የሚከፍሉበት አማራጭ ባንኩ ማዘጋጀቱንም ኦቦ ተፈሪ ጠቁመዋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የንግድ ሥራ ዘርፍ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ለማ ያዴቻ በበኩላቸዉ፤ በኦሮሚያ ባንክ እና በኳንተም ቴክኖሎጂ የቀረበዉ የክፍያ መፍትሄ፤ የአየር መንገዱ ደንበኞች በገንዘብ እጥረት ምክንያት ከጉዞ እቅዳቸው እንዳይስተጓጎሉ የሚረዳ ፍቱን አማራጭ ነዉ ብለዋል።

የኳንተም ቴክኖሎጂ መስራች እና ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ሶፎንያስ እምቢበል ባስተላለፉት መልዕክት ተቋሙ ለሀገራችን ዲጂታል ዘርፍ እድገት ከማበርከቱም በተጨማሪ በተለያዩ ዘርፎች ችግር ፈቺ የሆነ የቴክኖሎጂ ዉጤቶችን እያበረከተ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ኦሮሚያ ባንክ ዘመኑ በደረሰበት የቴክኖሎጀ ዉጤቶች የፋይናንስ እንቅስቃሴ ከማሳለጡ በተጨማሪ ለህበረተሰቡ አዳዲስ የፋይናንስ አማራጮችን እያቀረበ ይገኛል፡፡

Pin It on Pinterest

Share This

Share This

Share this post with your friends!

Share This

Share this post with your friends!

×