1. News and Updates
  2. ኦሮሚያ ባንክ ለተለያዩ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች የአምስት ሚልዮን ብር ድጋፍ አደረገ

ኦሮሚያ ባንክ የ2018 ዓ.ም የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለሀገር በቀል ግብረ ሰናይ ድርጅቶች የድጋፍ መርሃ ግብር አካሄዷል።

ኦሮሚያ ባንክ ከተቋቋመለት ተልዕኮዎች መካከል በተለያዩ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም በተፈጥሮ እና ሰዉ ሰራሽ ችግሮች ተጋላጭ ለሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ወገንተኝነቱን በማሳየት ማህበራዊ ኃላፊነቱን መወጣት ነዉ።

በዚህ መርሃ ግብር ድጋፍ የተደረገላቸዉ ድርጅቶች፦

1. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን 1,000,000.00 ብር

2. አበበች ጎበና የበጎ አድራጎት ድርጅት 1,000,000.00 ብር

3. የኩላሊት ህመምተኞች እጥበት በጎ አድራጎት ድርጅት 1,000,000.00 ብር

4. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምገባ ማዕከል 500,000.00 ብር

5. ኦዳ አዳሪ ትምህርት ቤት 500,000.00 ብር

6. ተስፋ አዲስ የህጻናት የካንሰር ህሙማን ማዕከል 500,000.00 ብር

7. ሰበታ የአይነ ስዉራን ትምህርት ቤት 500,000.00 ብር ድጋፍ ተደርጓላቸዋል።

የኦሮሚያ ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ ኦቦ ተፈሪ መኰንን በድጋፍ መርሐ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ፣ ባንኩ 1447ኛዉን የረመዳን ወር ምክንያት በማድረግ ለተለያዩ ሀገር በቀል ድርጅቶች ተመሳሳይ ድጋፍ ማድረጉን አስታዉሰዉ፤ በዛሬዉ ዕለትም አብይ ጾምን ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ማህበራዊ ችግር ያለባቸዉን ዜጎች ለሚረዱ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ አጋርነታችንን የምንገልጽበት መርሀ ግብር ነዉ ብለዋል፡፡

ድጋፉም ከበዓል መዋያ በዘለለ፥ የተረጂ ወገኖቻችን ቀጣይ ህይወት የሚሻሻልበት እንደሚሆን በመግለጽ፤ ባንካችን ለድርጅቶቹ ከአደራ ጭምር ድጋፍ ያደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በዚህ አጋጣሚም ለመላዉ የክርስትና እምነት ተከታዮች መጪውን የትንሳኤ በዓል አስመልክቶ፤ የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመጨረሻም የግብረ ሰናይ ድርጅቶቹ የስራ ኃላፊዎች እና ተወካዮች ባንካችን ላደረገላቸዉ ድጋፍ አመስግነዉ፣ ይህ ድጋፍ ለምንሰራዉ ሰብአዊ ስራ ትልቅ ስንቅ እና ማበረታቻ የሚሆነን ነዉ ብለዋል፤ አያይዘውም ሌሎች ባንኮች የኦሮሚያ ባንክን ፈላግ እንዲከተሉ ጥሪ አቅርበዋል::

Pin It on Pinterest

Share This

Share This

Share this post with your friends!

Share This

Share this post with your friends!

×