1. News and Updates
  2. ኦሮሚያ ባንክ ለዲቦራ ፋውንዴሽን የገንዘብ ድጋፍ አበረከተ።

ድጋፉን ለፋውንዴሽኑ መስራችና የቦርድ ሊቀመንበር ክቡር ኦቦ አባዱላ ገመዳ እና ለዲቦራ ፋውንዴሽን ከፍተኛ የስራ አመራር አባላት ያበረከቱት የኦሮሚያ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ ክቡር ኦቦ ተፈሪ መኮንን ናቸው።

በመርሐ ግብሩ ማስጀመሪያ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት ኦቦ ተፈሪ መኮንን፤ የተደረገው ድጋፍ ፋውንዴሽኑ የአዕምሮ ዕድገት ውስንነት ያለባቸው ሕፃናት ላይ ከሚያከናውናቸው በጎ ተግባራት ጎን ለመቆም የታሰበ መሆኑን በማንሳት፤ ባንካችን ለወደፊቱም ፋውንዴሽኑ ከሚሰራቸው ምግባረሰናይ ተግባሮች ጎን በመቆም አጋርነቱን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። አክለውም የባንካችን ሰራተኞች ሁሉ የፋውንዴሽኑ አባል በመሆን ድጋፋቸውን ማጠናከር እንዳለባችውም አስገንዝበዋል፡፡

የዲቦራ ፋውንዴሽን መስራችና የቦርድ ሊቀመንበር ክቡር ኦቦ አባዱላ ገመዳ በበኩላቸው፤ ለፋውንዴሽኑ ለተደረገው ድጋፍ ባንኩን በማመስገን የአእምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ሕፃናት ድጋፍ እና ክብካቤ ከተደረገላቸው በሀገር ግንባታ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ማድረግ የሚችሉ ዜጎች ሰለሆኑ፣ ሁሉም በሚችለው እነዚህን ሕፃናት መደገፍ እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡

ዲቦራ ፋውንዴሽን በአእምሮ እድገት ውስንነት ላይ የሚሰራ ግብረሰናይ ድርጅት ሲሆን፤ አላማውም የአእምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸውን ሕፃናት ድጋፍ እና ክብካቤ ማድረግ ነው። ኦሮሚያ ባንክ እንደ ወትሮው ሁሉ ማህበራዊ ህላፊነቱን ለመወጣት እና ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች ለመድረስ፤ ለበርካታ ሀገር በቀል ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ድጋፍ እያበረከተ ይገኛል።

Pin It on Pinterest

Share This

Share This

Share this post with your friends!

Share This

Share this post with your friends!

×