1. News and Updates
  2. ኦሮሚያ ባንክ “ተደራሽ የብድር አገልግሎት ለሁሉም ዜጎች” በሚል መሪ ቃል ለአንድ ወር የሚቆይ የሚልኪ ዲጂታል የብድር አገልግሎት የገበያ ንቅናቄ አስጀመረ፡፡

የንቅናቄው የማስጀመሪያ መርኃ-ግብርን በንግግር የከፈቱት የኦሮሚያ ባንክ የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት ቺፍ ኦፊሰር ኦቦ እርስቴ ወ/ማርያም፤ ሚልኪ ዲጂታል የብድር አገልግሎት፤ በዋስትና እጦት ምክንያት ከፋይናንስ አቅርቦት ርቀዉ የቆዩ በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡ የባንኩን ማስያዣ አልባ የብድር አገልግሎት ለሰፊዉ ማህበረሰብ ለማዳረስ እና የፍይናንስ አካታችነትን ለማረጋገጥ ለአንድ ወር የሚቆይ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርኃ ግብር መጀመሩንም አብስረዋል፡፡

የኳንተም ቴክኖሎጂ መስራች እና ማኔጂንግ ዳይሬክተር ኦቦ ሶፎንያስ እምቢበል በበኩላቸዉ ተቋማቸዉ ከባንኩ ጋር በመተባበር ስራ ላይ ያዋለዉ ሚልኪ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎችን የብድር ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረግ መልካም ዉጤት እያስመዘገበ ይገኛል ብለዋል፡፡ ሚልኪ ዘመኑን የዋጀ የሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት ቴክኖሎጂ በመጠቀም የብድር አሰጣጡን ስራ እያሳለጠ ነዉ ያሉት ኦቦ ሶፎኒያስ ሁሉም ማህበረሰብ እንዲጠቀም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ሚልኪ ዲጂታል የብድር አገልግሎት ገና ስራ ከጀመረ 100 ቀናት ዉስጥ ለ75ሺ ዜጎችን ያለምንም ማስያጃ ብድር በመስጠት ተጠቃሚ በማድረግ ከ250 ሚሊዮን ብር በላይ አቅርቧል።

Pin It on Pinterest

Share This

Share This

Share this post with your friends!

Share This

Share this post with your friends!

×