ሰምምነቱን የፈረሙት የኦሮሚያ ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኦቦ ተፈሪ መኮንን እና በቪዛ ኢንኮርፖሬትድ የምስራቅ አፍሪካ ቀጠና እና የኢትዮጵያ ሥራ አስከያጅ ኦቦ ያሬድ እንዳለ ናቸዉ፡፡
በስምምነቱ ላይ የኦሮሚያ ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኦቦ ተፈሪ መኮንን ባስተላለፉት መልዕክት ኦሮሚያ ባንክ ለደንበኞቹ ዘመኑን የዋጀ፤ ምቹ እና ቀለጣፋ ዓለም አቀፍ የክፍያ ካርድ አገልግሎቶችን ለማስፋፋት ለሰነቀዉ እቅድ ይህ አጋርነት እንደ ተጨማሪ ጉልበት ይቆጠራል ብለዋል፡፡
በቪዛ ኢንኮርፖሬትድ የምስራቅ አፍሪካ ቀጠና እና የኢትዮጵያ ሥራ አስከያጅ ኦቦ ያሬድ እንዳለ በበኩላቸዉ ቪዛ ባካበተዉ አለም አቀፍ ልምድ ፤ የሀገራችን የክፍያ ስራዓት ለማዘመን ከኦሮሚያ ባንክ ጋር አጋርነት በመፍጠሩ እጅግ ደስ ይለዋል ብለዋል፡፡
ይህ ስምምነት የኦሮሚያ ባንክ ደንበኞች ወደ ውጭ ሀገር በሚጓዙበት ወቅት ምንም ዓይነት የውጭ ሀገር ጥሬ ገንዘብ መያዝ ሳያስፈልጋቸው በኦሮሚያ ባንክ ዓለም አቀፍ ክፍያ ቪዛ ካርድ በመጠቀም በመላው የዓለም ሀገራት በሚገኙ የኤቲኤም እና የክፍያ መፈፀሚያ ማሽኖች (POS) በቀላሉ ክፍያ መፈፀም እና የሚፈልጉትን አገልግሎት ማግኘት የሚያስችላቸውን ሁኔታ ያመቻቻል ተብሏል፡፡
በተጨማሪም አገልግሎቱ በአሁኑ ወቅት በዓለማችን እየተስፋፋ በመጣው ኢ-ኮሜርስ እና የበይነ መረብ አማካኝነት ግብይት እና ክፍያ መፈፀም እንዲሁም በውጪ ሃገር ለሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዳያስፖራዎች ለቤተሰቦቻቸው እና ለወዳጆቻችው ተጨማሪ የዲጂታል ኃዋላ መላኪያ አማራጭ በመሆን ካሉበት ቦታ ሆነው በማንኛውም ጊዜ ደህንነነቱ በተጠበቀ መንገድ በፍጥነት ገንዘብ መላክ ያስችላቸዋል፡፡

