ኦሮሚያ ባንክ ከሳንቲም ፔይ ጋር በመሆን የግብይት ስርዓቱን ያዘምናል የተባለው አዲስ የዲጂታል ክፍያ ስርዓት በተለያዩ የሀገራችን ከተሞች ማስተዋወቁን በመቀጠል በዛሬ ዕለትም የባንካችን ከፍተኛ ዓመራሮች እና ደንበኞች በተገኙበት በጂማ ከተማ ይፋ ተደርጓል።
ኦሮሚያ ባንክ እና ሳንቲም ፔይ በጋራ በመሆን ለአገልግሎት ዝግጁ ያደረጉት አዲስ የዲጂታል ክፍያ ስርዓት ከየትኛውም የባንክ ቁጥር በስልክዎ ካሜራ በመጠቀም QR ስካን በማድረግ ብቻ የትኛውንም ክፍያ በቀላሉ እንዲፈጽሙ ያስችላል።
ሁለቱ ተቋማት በጋራ በመሆን ቀደም ሲልም በጅግጅጋ፣ ድሬዳዋ፣ ሀዋሳ እና ሻሻማኔ ከተሞች ዘመናዊ የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት ማስተዋወቃቸዉ ይታወሳል፡፡

