በዚህ መርሃ ግብር ላይ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የኦሮሚያ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኦቦ ተፈሪ መኰንን በአለም አቀፍ እና ሀገር አቀፍ ሁኔታዎች የፋይናንስ ዘርፉ ተለዋዋጭና ተገማች ባልሆነበት ሁኔታ ዉስጥ ባንካችን ፈተናዎችን ተቋቁሞ የበጀት ዓመቱን በአመርቂ ዉጤት ማጠናቀቁን ገልፀዋል፡፡ በተለይም ባንኩ በታሪኩ ከፍተኛ የተባለዉን የተቀማጭ ገንዘብ ማሰባሰብን ጨምሮ በሁሉም ቁልፍ መለኪያዎች ከፍተኛ ስኬት መመዝገቡን ኦቦ ተፈሪ ገልፀዋል፡፡
ኦቦ ተፈሪ አክለዉም ዘንድሮ ባንካችን ላስመዘገዉ አመርቂ ዉጤት የማይተካ ሚና ለተጫወቱት ለክቡራን ደንበኞቹ ፣ ለባለአክሲዮኖች ፣ ለሥራ አመራር ቦርድ አባላት ፣ ለባንኩ ከፍተኛ እና መካከለኛ ዓመራሮች እንዲሁም ለመላዉ የባንኩ ሰራተኞች ከፍ ያለ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በመቀጠልም የ2026/2027 የበጀት ዓመት መጀመሪያ ቀን ላይ እንደመሆናችን መጠን በአዲስ ጉልበት እና በከፍተኛ ተነሳሽነት ስሜት አሁን የተመዘገበዉን ዉጤት እንደ መስፈንጠሪያ በመጠቀም ለተሻለ ስኬት በየደረጃዉ ያሉ የባንካችን ሰራተኞች ከወዲሁ ርብርብ እንዲያደርጉ በማሳሰብ መልካም የ2026/2027 በጀት ዓመት እንዲሆን ተመኝተዋል::

