1. News and Updates
  2. ኦሮሚያ ባንክ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባዘጋጀው የሐዋላ ፍሰት ግንዛቤ ማስጨበጫ አውደ ርዕይ ላይ ተሳትፏል።

የግንዛቤ ማስጨበጫ አውደ ርዕይ

ባንካችን ከሀገር ውጭ ለሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያዊያንን ማዕከል ያደረጉ የባንክ አገልግሎቶችን ለአውደ ርዕይው ተሳታፊዎች አስተዋውቋል።

በእስካይላይት ሆቴል በተዘጋጀው አውደ ርዕይ ላይ የብሔራዊ ባንክ ገዢ አቶ ማሞ ምህረቱ ፣ የባንካችን ዋና አስፈፃሚ አቶ ተፈሪ መኰንን ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖን ጨምሮ የበርካታ ባንኮች ከፍተኛ ዓመራሮች እንዲሁም በውጭ ሀገር የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ተሳትፈዋል።

ኦሮሚያ ባንክ ዜጎቻችን ከባህር ማዶ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ከእኛ ጋር በሚሰሩ ገንዘብ አስተላላፊ ወኪሎች በኩል የሚልኩትን የውጭ ሀገር ገንዘብ በታማኝነት በማድረስ መልካም ስም አፍርቷል።

በተጨማሪም ባንኩ የዲያስፓራውን ማህበረሰብ በልዩነት ተጠቃሚ የሚያደርጉ በርካታ የባንክ አገልግሎቶች ቀርፆ ተግባራዊ እያደረገ ነው።

Pin It on Pinterest

Share This

Share This

Share this post with your friends!

Share This

Share this post with your friends!

×