በዚህ የሰደቃ መርሃ-ግብር ላይ የባንካችን ዋና ስራ አስፈፃሚ ኦቦ ተፈሪ መኰንን፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ተወካይ፣ የባንካችን ከፍተኛ የአመራር አባላት፣ ዑለማኦች እና ጥሪ የተደረገላቸው የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ተገኝተዋል፡፡
የረመዷን ወር የመተዛዘን እና የመረዳዳት ወር በመሆኑ፣ ኦሮሚያ ባንክ በአምስት የበጎ አድራጎት ድርጅቶች በኩል ለተቸገሩ ወገኖች ይዉል ዘንድ የገንዘብ ድጋፍ አበርክቷል፡፡ በዚህ መሠረትም፣ ለባቡል ኸይር የበጎ አድራጎት ድርጅት፣ ለአማና የልማት ማህበር፣ ለየሲር ለና የበጎ አድራጎት ድርጅት፣ ለሙፈቲ ዳዉደ የኬሚሴ ወጣቶች የበጎ አድራጎት ድርጅት፣ እና ለወንድም ካሊድ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች የገንዘብ ድጋፍ ተበርክቷል፡፡
የኦሮሚያ ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኦቦ ተፈሪ መኰንን፣ ባንካችን የሸሪዓዉን እሴቶች ያከበሩ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ከመስጠት ባለፈ፤ ድጋፍ ከሚያስፈልጋቸው ዜጎች ጎን በመቆም ማህበራዊ ሀላፊነቱን በሚገባ እየተወጣ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የገንዘብ ድጋፍ የተበረተከላቸው ተቋማት ለዚህ እማኞች መሆናቸዉንም በማስገንዘብ የተደረገው ድጋፍ ተጠቃሚዎች ጋር በአግባቡ እንዲደርስ የአደራ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ተወካይ ሼህ መሀመድአሚን ሰይድ በበኩላቸዉ፣ ኦሮሚያ ባንክ ከምሰረታው ጀምሮ በህዝበ ሙስሊሙ ማህበረሰብ በመልካም ተግባሩ ይታወቃል በማለት ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች ለተበረከተው ሰደቃ ባንኩን አመስግነዋል።
የበጎ አድራጎት ድርጅቶችም፣ የተበረከተላቸው ሰደቃ በሀገራችን ፈር ቀዳጅ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ባለበት የሆነውን ኦሮሚያ ባንክን በማመሰገን፤ መሰል ተቋማትም ይህንን አርአያነት እንድከተሉ ጥሪ አቅርበዋል።

