በዚህ የሰደቃ መርሃ ግብር ድጋፍ የተደረገላቸዉ ድርጅቶች መካከል፦
1. አወሊያ የእርዳታና ልማት ድርጅት አንድ ሚሊዮን ብር፣
2. አል አማና አብዱልፈታ ፋዉንዴሽን 750 ሺህ ብር፣
3. ኢህሳን ፋዉንዴሽን 500 ሺህ ብር፣
4. ኡሙት ኢስላሚክ የበጎ አድራጎት ድርጅት 500 ሺህ ብር፣
5. ኤጌሬፍ የበጎ አድራጎት ድርጅት 500 ሺህ ብር እንዲሁም
6. መርሃባ ኸደም ኢስላሚክ ማህበር 500 ሺህ ብር ድጋፍ ተደርጎላቸዋል፡፡
የኦሮሚያ ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ ኦቦ ተፈሪ መኰንን በሰደቃ መርሃ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ፣ ባንኩ ለማህበረሰባችን ቀልጣፋ የባንክ አገልግሎት ከመስጠት ባሻገር ማህበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት ድጋፍ ከሚሹ ወገኖች ጎን በመቆም ይታወቃል።የዛሬው የሰደቃ መርሃ ግብርም ለዚሁ ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠ/ም/ቤት ተወካይ እና የግብረ ሰናይ ድርጅቶቹ የስራ ኃላፊዎች በሰደቃ ርክክቡ ወቅት ባንኩ ላደረገዉ ድጋፍ አመስግነዉ ፣ ሌሎች ተቋማትም ይህንን የባንኩን አርአያነት በመከተል ለችግር የተጋለጡ ወገኖቸን የመርዳት እና የመንካባከብ በጎ ስራን እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

