1. News and Updates
  2. ኦሮሚያ ባንክ 2024/2025 የበጀት ዓመትን በአስደማሚ ዉጤት ማጠናቀቁን አስመልክቶ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፈ፡፡
ባንኩ በተጠናቀቀዉ የበጀት ዓመት በታሪኩ የላቀ ዉጤት ማስመዝገቡን ምክንያት በማድረግ ፤ ለዉድ ደንበኞቹ፥ለስራ ዓመራር ቦርድ፣ ለማኔጅመንቱ ፥ ለመላዉ ሰራተኞቹ እና ደንበኞቹ የእንኳን ደስ አላችሁ መልክት አስተላልፏል፡፡ በዋናዉ መስሪያ ቤት በተዘጋጀዉ የምስጋና መርኃ-ግብር ላይ የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኦቦ ተፈሪ መኰንን፤ ያለፈውን የበጀት ዓመት  በርካታ ውጫዊ እና ውስጣዊ ፈተናዎችን ተቋቁመን  አስደማሚ ዕድገት ለማስመዝገብ ችለናል ብለዋል። ኦቦ ተፈሪ አክለዉም፥ በዲጅታል ተደራሽነት፣ በብድር አመላለስ፣ በጤናማ ብድር ምጣኔ፣ በፕሮጀክት አፈጻጸም፣ በአገልግሎት አሰጣጥ ፣ በህግ አክባሪነት የነበረንን ጥንካሬ ይበልጥ አሻሽለን መልካም ስማችንን የበለጠ በመገንባት አስደማሚ ትርፋማነት ማስመዝገብ ችለናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡ ለዚህ ስኬት አስተዋጽኦ ላበረከቱ ባለድርሻ አካላት፤ ዉድ የደንበኞች፣ የስራ ዓመራር ቦርድ አባላት ፣ ማኔጅመንት  እና የባንኩን መላ ሰራተኞች አመስግነዋል፡፡ በመጨረሻም ኦቦ ተፈሪ ባስተላለፉት መልዕክት፤ቀጣዩ የበጀት ዓመት ባንካችን የነደፈው 4ኛው የ3 ዓመት መሪ ዕቅድ ትግበራ የመጀመሪያ ዓመት በመሆኑ የተሻለ ውጤት በማምጣት ባንካችን በተያያዘው የከፍታ ፍጥነት እንዲጓዝ ብሎም ወደሚገባው የገበያ ድርሻ በማምጣት መላዉ የባንኩ ሰራተኛ ጠንክሮ እንዲሰራ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Pin It on Pinterest

Share This

Share This

Share this post with your friends!

Share This

Share this post with your friends!

×