1. News and Updates
  2. ኦሮሚያ ባንክ 42ኛውን የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ዋና አጋር መሆኑን ሲገልፅ ታላቅ ደስታ ይሰማዋል፡፡

ኦሮሚያ ባንክ ቀልጣፋ እና ዘመናዊ የባንክ አገልግሎት ከመስጠት ባሻገር የሀገራችንን ስም እና ሰንደቅ አላማ በአለም አደባባይ ከፍ አድርገዉ የሚያሳዩ ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት የስፓርቱን ዘርፍ እየደገፈ ይገኛል፡፡

በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት የተካሄደዉ 42ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ሻምፒዮና በተለያዩ ርቀቶች ዉድድር የተካሄደ ሲሆን የባንካችን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኦቦ ተፈሪ መኮንን በዝግጅቱ ላይ በመገኘት ለአሸናፊ አትሌቶች ሽልማት አበርክተዋል፡፡

በውድድሩ ላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮማንደር ስለሺ ስህንን ጨምሮ ብርቅዬ የሀገራችን አትሌቶች እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል፡፡ ባንካችን መሰል ውድድሮችን በመደገፍ ለሀገራችን መልካም ስም እና ዝና በጎ ተፅዕኖ በሚፈጥሩ እስፖርታዊ ኩነቶች ላይ አጋርነቱን አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

Pin It on Pinterest

Share This

Share This

Share this post with your friends!

Share This

Share this post with your friends!

×