በሥነ-ሥርዓቱ ላይ በመገኘት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የኦሮሚያ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኦቦ ተፈሪ መኮንን፤ ሴቶች የባንካችን ስኬት የጀርባ አጥንት ናቸዉ ብለዋል፡፡ ሴቶችን ማብቃት እና መደገፍ ማህበረሰቡን መደገፍ ነዉ ያሉት ኦቦ ተፈሪ፤ ባንካችን የሴቶችን እኩልነት እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ጠንክሮ ይሰራል ብለዋል፡፡ በባንካች የሴቶች ተሳትፎ እየጨመረ መምጣቱን በመጠቆም።
በኦሮሚያ ባንክ ዋና መስሪያ ቤት በተከበረዉ ዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን መድረክ ላይ፤ በዘንድሮ ዓመት ወደ ከፍተኛ ዓመራር ለተቀላቀሉ ሴት ከፍተኛ ዓመራሮች አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡ ልምድ እና ተሞክሯቸዉንም አከፈለዋል፡፡
“ለማትረፍ አበርክቱ” በሚል መሪህ ቃል እየተከበረ የሚገኘዉ አለም አቀፉ የሴቶች ቀን ዘንድሮ ለ115ኛ ጊዜ እየተከበረ ይገኛል፡፡

