1. News and Updates
  2. የኦሮሚያ ባንክ ዓመታዊ የሥራ አመራር አባላት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ

ዓመታዊ የሥራ አመራር አባላት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ

በኢንተር ለግዥሪ ሆቴል ሲካሄድ የነበረው የኦሮሚያ ባንክ ዓመታዊ የሥራ አመራር አባላት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ ለሚቀጥለው የሥራ ዓመት አቅጣጫ በማስቀመጥ ተጠናቋል።

በዚህ ዓመታዊ ግምግማ ላይ የቀጠና ፅ/ቤቶች እና የቅርንጫፎች ባንኮች የስራ አፈፃፀም ሪፓርት ቀርቦ ጥልቅ ውይይት ተካሂዶባቸዋል።

በአዲሱ የበጀት ዓመት የባንኩን የአገልግሎት አሰጣጥ ወደ ላቀ ደረጃ በማሸጋገር ለደንበኞች ምቹ እና ቀልጣፋ የባንክ አገልግሎት ለመስጠት ትኩረቱን የሀብት ማስባሰብ ያደረገ የጋራ አቋም ተይዟል።

በቅርንጫፎች፣ በቀጠና ጽ/ቤቶች እና በባንኩ ሰራተኞች መካከል የውድድር መንፈስ ለማስረፅ በዋና ስራ አስፈፃሚያችን በአቶ ተፈሪ መኮንን ሀሳብ አመንጪነት ሲካሄድ የቆየው የCEO CHALLENGE የፕሬዝዳንሺያል አዋርድ  የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ የቀጠና ፅ/ቤቶች፣ ቅርንጫፎች እና ሰራተኞች ሽልማት እና ዕውቅና ተሰጥቷል።

Pin It on Pinterest

Share This

Share This

Share this post with your friends!

Share This

Share this post with your friends!

×