የኦሮሚያ ባንክ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች እና ሰራተኞች የቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች በአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብሩ ላይ ተሳተፈዋል።
የኦሮሚያ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኦቦ ተፈሪ መኮንን በመርሃ-ግብሩ ላይ ባስተላፉት መልዕክት ባንካችን ማህበራዊ ሀላፊነቱን ለመውጣት ላለፉት በርካታ ዓመታት ሰራተኞቹን በማሳተፍ በችግኝ ተከላ ላይ በስፋት ሲሳተፍ ቆይቷል ብለዋል። በቀጣይም ባንኩ በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በንቃት መሳተፉን ይቀጥላል ብለዋል፡፡
የአከባቢ እና የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራ የኦሮሚያ ባንክ ተቋማዊ ኃላፊነት ነው ያሉት ኦቦ ተፈሪ፤ የተተከሉትን ችግኞችን መንከባከብ ደግሞ ቀጣይ ስራ መሆን እንዳለበትም አሳስበዋል።
የችግኝ ተከላ መርኃ-ግብሩ ተሳተፊዎች በኦሮሚያ ባንክ አየተገነባ ያለውን የልህቀት እና የኮንቬንሽን ማዕከል ሁለተኛ ምዕራፍ ግንባታ የሆነውን ባለ 11 ወለሉን ዘመናዊ የንግድ ማዕከል ጎብኝቷል፡፡

