በመሀል ፊንፊኔ ጎማ ቁጠባ አከባቢ የማጠቃለያ ሥራው እየተገባደደ የሚገኘው የኦሮሚያ ባንክ የሽግግር ዋና መስሪያ ቤት ሰማይ ጠቀስ ህንፃ፤ የውስጠኛው የፓርቲሽን ስራ ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል። የማጠቃለያ ግንባታ ወሳኝ ምዕራፍ የሆነው የኤሌክትሮ መካኒካል ስራ 80 በመቶ ተገባዷል። ለህንፃው ተብለው ከሀገር ውጪ የተመረቱ የከርቴን ዎል እና የመስታወት ምርቶች ሙሉ በሙሉ ተጠናቀው ምርቶቹ የግንባታ ቦታ ላይ ደርሰዋል። በጥቂት ቀናት ወስጥም የውጨኛው ክፍል መስታወት የማልበስ ሥራ ይጀመራል።
በጉብኝቱ ላይ የባንካችን የዳይሬክተሮች ሰብሳቢ ዶ/ር አሰፋ ስሜ ፤ የባንካችን ዋና ስራ አስፈፃሚ ኦቦ ተፈሪ መኮንን፤ ምክትል ቦርድ ሰብሳቢ አቶ እሸቱ ዘለቅ እና የባንካችን የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል የተከበሩ ዶ/ር ኢንጂነር እሸቱ ተመስገንን ጨምሮ ከፍተኛ የባንካችን አመራሮች ተገኝተዋል።
ይህ ባለ 35 ወለል ግዙፍ ህንጻ በ2200 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ ሲሆን፤ ህንፃዉ በያዘዉ ገዢ እና ከፍታ ቦታ መዲናችንን ሙሉ በሙሉ በማሳየት፤ ለከተማችን አዲስ የእይታ አድማስ እና ዉበት እንዲሁም ለሀገራችን ተጨማሪ ኩራት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

