የግብይት ስርዓቱን ያዘምናል የተባለው አዲስ የዲጂታል ክፍያ ስርዓት በሻሻማኔ ከተማም ይፋ ተደረጓል!
ኦሮሚያ ባንክ ከሳንቲም ፔይ ጋር በመሆን በተለያዩ የሀገራችን ከተሞች አዲስ የዲጂታል ክፍያ ስርዓት ማስተዋወቁን ቀጥሏል።
በዛሬ ዕለትም በሻሸመኔ ከተማ የአገልግሎት ሰጭ ድርጅቶች፣ ደንበኞች እና የተለያዩ የንግድ ተቋማት በተገኙበት ይፋ ተደርጓል!
ኦሮሚያ ባንክ እና ሳንቲም ፔይ በጋራ በመሆን ቀደም ሲልም በጅግጅጋ፣ ሐዋሳ እና ድሬዳዋ ከተሞች ዘመናዊ የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት ማስተዋወቃቸዉ ይታወሳል፡፡

